“ኢትዮጵያ ለሕልውናዋና ለሀገራዊ ጥቅሟ ስትል የኤርትራን የጥፋት እንቅስቃሴ ለመግታት እርምጃ መውሰድ አለባት ”-ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ‼️
የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፣ ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ የምታደርገውን የጥፋት እንቅስቃሴ ካላቆመች ኢትዮጵያ ለሕልውናዋና ለሀገራዊ ጥቅሟ ስትል የችግሩን ሥረ መሠረት ለመንቀል ከመንቀሳቀስ ውጪ ሌላ አማራጭ እንደማይኖራት ተናገሩ። ሆኖም የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ በሰላማዊና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ መፈታት እንዳለበት አሳስበዋል። ዶ/ር ሙላቱ በሰጡት መግለጫ፣ የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ ታሪካዊ መብትን፣ የኢኮኖሚ ሕልውናንና የቀጣናውን ሰላም የሚመለከት መሠረታዊ አጀንዳ መሆኑን ገልጸዋል። ግብጽ ኢትዮጵያ በድህነትና በግጭት ውስጥ እንድትቆይ የማድረግ የቆየ ፖሊሲ እንዳላት የጠቀሱት ዶ/ር ሙላቱ፣ በ1960ዎቹ የኤርትራ ነፃነት ግንባርን በመደገፍ ኢትዮጵያ የባሕር በር አልባ እንድትሆን ዋነኛ ሚና ተጫውታለች ብለዋል።