የባሕር ኃይል አዛዡ፣ "ኢትዮጵያ ወደ ወደብ መመለሷ የማይቀር" ስለሆነ ከቀጠናው አገራት ጋር በቅርበትና በንግግር መሥራት አስፈላጊ መሆኑን ጥሪ አቀረቡ‼️
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20 ቀን 2019 ዓ.ም. ፦ የኢትዮጵያ ወደ ባሕር በር ባለቤትነት የመመለስ ጉዳይ አይቀሬ በመሆኑ ከጎረቤት አገራት ጋር በቅርበት መሥራት እና በውይይት መመራራት አስፈላጊ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አዛዥ ምክትል አድሚራል ክንዱ ገዙ ገለጹ። አዛዡ ጥሪውን ያቀረቡት በቀጣናዊ የባሕር ላይ ደኅንነት ዙሪያ ጠንካራ ትብብርና ውይይት እንዲደረግ ባሳሰቡበት ወቅት ነው። እንደ አገሪቱ መከላከያ ሠራዊት መረጃ፤ ምክትል አድሚራል ክንዱ ይህን የተናገሩት የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ባዘጋጀው ቀጣናዊ የባሕር ደኅንነት የምክክር መድረክ ማጠቃለያ ላይ ነው። @Seledadotio