ChatGPT የሰጠው የተሳሳተ የሕክምና ምክር ለቀድሞ የአማዞን ሰራተኛ ህልፈተ ህይወት ምክንያት ሆነ!
በአሜሪካ ሲያትል ከተማ የምትኖር የ31 ዓመት ወጣት እና የቀድሞ የአማዞን ሶፍትዌር ኢንጂነር ቦወን ዋን፣ የChatGPT የሕክምና ምክርን በመከተል የመጥበብ (የ የሚጥል) በሽታ መድኃኒቱን መጠን በመቀነሱ ህይወቷ አልፏል። ጉዳዩን አስመልክቶ የሟች ቤተሰቦች በኦፕንኤአይ (OpenAI) እና በዋና ስራ አስፈፃሚው ሳም አልትማን ላይ ክስ መስርተዋል። ዋን ሥራዋን ካጣች በኋላ የጎንዮሽ ጉዳቶችን በመፍራት ዶክተር ማማከር ሳይኖርባት የመድኃኒቱን መጠን እንዲቀንስ አርቴፊሻል ኢንተለጀንቱ አበረታቷል ተብሏል። የኦፕንኤአይ ቃል አቀባይ ድሩ ፑሳቴሪ ክስተቱን እጅግ አሳዛኝ ሃዘን ብለውታል። ይሁን እንጂ ቴክኖሎጂው የባለሙያዎችን ምትክ ሊሆን እንደማይችል በመግለጽ ጉዳዩ በህግ አግባብ እየተጣራ ይገኛል።