← All news
News Oct 30, 2026 · 8d ago

ሳውዲ አረቢያ ከኢትዮጵያ የሚደረገውን የቤት ሠራተኞች ቅጥር አለመሰረዟን ገለጸች

የሳውዲ አረቢያ የሰው ኃይል እና ማኅበራዊ ልማት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የሚደረገውን የቤት ሠራተኞች ቅጥር ውል ሙሉ በሙሉ ሰርዟል ተብሎ የሚናፈሰውን ወሬ ማስተባበሉን ሳውዲ ጋዜጣ ዘግቧል።   ሚኒስቴሩ፤ በሙሳነድ የዲጂታል መድረክ በኩል የሚደረገው የቅጥር ሒደት መቋረጡንና ይህም ከ30 በመቶ የዋጋ ጭማሪ ጋር የተያያዘ ነው ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሐሰት መሆኑን አመልክቷል።   ሚኒስቴሩ እንዳብራራው፤ በውጭ አገር ያሉ የተወሰኑ የሠራተኛ አቅራቢ ኤጀንሲዎች ውላቸውን መወጣት ባለመቻላቸው ምክንያት በቁጥር ጥቂት የሆኑና የተጓተቱ ውሎች ብቻ እንዲሰረዙ የተደረገ ሲሆን፣ ይህም የደንበኞችን መብትና የአገልግሎቱን ጥራት ለመጠበቅ የተወሰደ ሕጋዊ እርምጃ ነው።   ከኢትዮጵያ የሚደረገው የቤት ሠራተኞች ቅጥር አገልግሎት አስቀድሞ በተቀመጠውና በጸደቀው የዋጋ ተመን መሠረት አሁንም በሥራ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።