← All news
News Oct 30, 2026 · 8d ago

የመንግሥት “ኮድ 4” ሰሌዳ ያላቸው ነባር ተሽከርካሪዎች እስከ ጥቅምት 30 አዲሱን “ETH” ሰሌዳ እንዲቀይሩ ተወሰነ

በፌዴራል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችና ተጠሪ ተቋማት ሥር የሚገኙና የመንግሥት “ኮድ 4” መለያ ሰሌዳ ያላቸው ነባር ተሽከርካሪዎች እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ ሰሌዳቸውን በአዲሱ “ETH” መለያ እንዲቀይሩ ትዕዛዝ መሰጠቱን አሐዱ ሬዲዮ ዘገበ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አዲሱን “ETH” የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ከሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለአዳዲስ ተሽከርካሪዎች ምዝገባ ተግባራዊ ማድረጉ ተገልጿል። አሁን ደግሞ አሰራሩን በማስፋት ነባር የመንግሥት ተሽከርካሪዎች ሰሌዳ የመቀየር ሥራ ተጀምሯል። አሐዱ ሬዲዮ ከሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ እንደዘገበው፣ የነባር “ኮድ 4” ተሽከርካሪዎች የሰሌዳ መቀየር አገልግሎት ከጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ተጀምሯል። አገልግሎቱም እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም. ብቻ የሚቆይ መሆኑ ተጠቁሟል። በመሆኑም የሚመለከታቸው የፌዴራል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችና ተጠሪ ተቋማት የተሽከርካሪ ፋይላቸው በሚገኝበት የባለሥልጣኑ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በአካል በመቅረብ ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ በፊት የሰሌዳ መቀየር አገልግሎቱን እንዲያገኙ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።