← All news
News Oct 30, 2026 · 8d ago

የትራንስፖርት ተቆጣጣሪ በመምሰል ሴት

አሽከርካሪን ለማገት የሞከረ ግለሰብ ተያዘ በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ተገኝ መውደድ የተባለ ግለሰብ አንፀባራቂ ልብስ ለብሶ የትራንስፖርት ተቆጣጣሪ በመምሰል አንዲትን ሴት አሽከርካሪ አታሎ መኪና ውስጥ በመግባት በሽጉጥ አስፈራርቶ ሊያግታቸው ሞክሯል። ተበዳይዋ በድፍረት መኪናውን እያሽከረከሩ የፖሊስ አባላትን ሲመለከቱ ባሰሙት የድረሱልኝ ጥሪ፣ ወንጀለኛው ተይዟል። ፖሊስ በተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት ባደረገው ፍተሻ ሽጉጥ፣ አንፀባራቂ ልብስ፣ ሳንጃ እና የተሰረቁ የኤሌክትሪክ ገመዶች አግኝቷል። ህብረተሰቡም አንፀባራቂ ልብስ ለብሰው ህጋዊ በሚመስሉ አካላት የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል የሰራተኞቹን መታወቂያ ማረጋገጥ እንዳለበት አሳስቧል።