← All news
News Oct 30, 2026 · 9d ago

አሳዛኝ ዜና፡ አርቲስት አንተነህ ተኸርቁ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ‼️

በበርካታ የኪነ-ጥበብ ሥራዎችና በስፖርት ዘርፍ በሚያሳየው ተሳትፎ በብዙዎች ዘንድ የሚታወቀው ወጣቱ አርቲስት አንተነህ ተኸርቁ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል። አርቲስቱ ከዚህ ቀደም በጽኑ ታሞ በነበረበት ወቅት፣ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያለ ምንም የዘርና የሃይማኖት ልዩነት ተባብሮለት አገግሞ ወደ ሥራው ተመልሶ የነበረ መሆኑ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ትላንትና ለሊት ሕይወቱ ማለፉ መረጋገጡ ቤተሰቦቹን፣ የሙያ አጋሮቹን እና አድናቂዎቹን ከፍተኛ ሐዘን ውስጥ ጥሏል።