← All news
News Oct 30, 2026 · 9d ago

Binance ከባድ ጥቃት ደረሰበት‼️

በዓለም ላይ ትልቁ የክሪፕቶ ንግድ መገበያያ የሆነው Binance ትናንት ሐሙስ ከፍተኛ የተባለ የሳይበር ጥቃት ተፈፅሞበታል። በዚህ የሳይበር ጥቃት Binance እስከ 6.3 ቢሊዮን (£4.7 ቢሊዮን) ዶላር እንዳጣ ቢቢሲ ዘግቧል። ይህ ጥቃት በዓለም ላይ እስካሁን ከተፈፀሙ ጥቃቶች ውስጥ ከፍተኛ ኪሳራ በማድረስ ቀዳሚ ሆኗል። የጥቃቱ ሰለባ የሆነውን የተወሰነ ገንዘብ ማገዱን Binance ያስታወቀ ሲሆን የግለሰቦች ንብረት ግን ደህንነቱ እንደተጠበቀ መሆኑን እና አሁን ላይ ማንኛውንም ግብይቶችን ለጊዜው አቋርጧል። በጥቃቱ ለተጎዱ ግለሰቦች ካሳ እከፍላለሁ ብሏል። ከጥቃቱ ጀርባ ሰሜን ኮሪያ እንዳለችበት እየተዘገበ ይገኛል።