← All news
News Oct 30, 2026 · 9d ago

«የ2018 የግብር ዘመን የደረጃ 'ሀ' የንግድ ትርፍ ግብር ማሳወቂያና መክፈያ ጊዜ ጥቅምት 30 መጠናቀቁ ታውቋል»

​የ2018 የግብር ዘመን የደረጃ "ሀ" ዓመታዊ የንግድ ትርፍ የማሳወቂያና የመክፈያ ጊዜ ጥቅምት 30/2019 ዓ.ም የሚጠናቀቅ መሆኑን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል። ​ግብር ከፋዮች በመጨረሻዎቹ ቀናት ከሚያጋጥሙ የሲስተም መጨናነቅ፣ ወረፋና መጉላላት እንዲሁም በወቅቱ ባለመክፈል ከሚመጣ ቅጣት ለመዳን ቀሪዎቹን ቀናት በመጠቀም ግብራቸውን በኦንላይን አሳውቀው እንዲከፍሉ ጥሪ መቅረቡ ታውቋል። ​ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮችን ዓመታዊ የንግድ ትርፍ ግብር የማሳወቅና የመክፈል ሂደት ሙሉ በሙሉ በበይነ-መረብ (ኦንላይን) እንዲሆን መደረጉ ተመላክቷል። ​በዚህም መሠረት ግብር ከፋዮች በአካል ወደ ቢሮ መምጣት ሳያስፈልጋቸው የሂሳብ መዝገቦቻቸውን በሲስተም አማካኝነት በመላክ እና የክፍያ ማዘዣ ሲደርሳቸው ክፍያቸውን በኦንላይን መፈጸም የሚችሉ መሆኑ ታውቋል። ​@Seledadotio