«በደቡብ ወሎ ዞን ሀይቅ ከተማ በሚገኝ የተፈናቃዮች ካምፕ ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተገለጸ»
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ሀይቅ ከተማ ጃሪ ተብሎ በሚጠራው የተፈናቃዮች መጠለያ ካምፕ ላይ በደረሰ ጥቃት በርካታ ሰዎች ሕይወታቸው ማጣቱ ከአካባቢው የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ። በግጭት ሳቢያ ከቀዬያቸው ተፈናቅለው በካምፑ ውስጥ ተጠልለው በነበሩ ዜጎች ላይ በደረሰው በዚህ ጥቃት ስለደረሰው የሞት እና የጉዳት መጠን ዝርዝር መረጃዎች እየተጣሩ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ @Seledadotio