← All news
News Oct 29, 2026 ¡ 9d ago

🚨 «የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎቹ ወደ አማራ፣ ትግራይ እና አፋር ክልሎች እንዳይጓዙ ዳግም ማሳሰቢያ መስጠቱ ታወቀ»

​በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን የጸጥታ ሁኔታ እየተከታተለ መሆኑን ገልጾ፣ የአሜሪካ ዜጎች በማንኛውም ምክንያት ወደ አማራ፣ ትግራይ እና አፋር በተለይም ወደ ሰሜን አፋር ክልሎች እንዳይጓዙ ጥብቅ ማሳሰቢያ መስጠቱ ይታወቃል፡፡ ​እንዲሁም የአሜሪካ ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝ ያሰቡ ካሉ በድጋሚ እንዲያጤኑት በብርቱ ያሳሰበ ሲሆን፣ በክልሎቹ በተለይም በትግራይ ግጭቱ ከመቀሌ ውጪ ባሉ አካባቢዎች እና በኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ማተኮሩንና የአክሱምና ሽሬ አየር ማረፊያዎች በረራዎች መቋረጣቸውን አስታውቋል፡፡ ​በሌላ በኩል በሞያሌ የተከሰተው ግጭት የመረጋጋት ምልክት ማሳየቱን የገለጸው ኤምባሲው፣ በኢትዮጵያ የጸጥታ ሁኔታ ላይ የተሳሳቱ መረጃዎች እየተሰራጩ በመሆናቸው ዜጎች መረጃዎችን ከአስተማማኝ ምንጮች እንዲያጣሩ እና ከወታደራዊ ሰፈሮች አቅራቢያ እንዲርቁ አሳስቧል። ​@Seledadotio