በአዲስ አበባ ዳቦ ቤቶች የ70 ግራም ዳቦ ዋጋ ላይ የ2 ብር ቅናሽ ተደረገ
ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ በነፃ ገበያ ሲሸጥ የቆየው የ70 ግራም ዳቦ ዋጋ ላይ ቅናሽ መደረጉን የአዲስ አበባ ዳቦ አምራቾች ማህበር አስታወቀ። ማህበሩ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በላከው ይፋዊ ደብዳቤ እንደገለጸው፣ ከክፍለ ከተሞች ከሚገኙ የዳቦ አምራች ማህበራት አመራሮች ጋር ሰፊ ውይይት ካካሄደ በኋላ አዲሱን የዋጋ ውሳኔ አሳልፏል። በዚህም መሠረት ቀደም ሲል በ15 ብር ይሸጥ የነበረው ባለ 70 ግራም ዳቦ ከአሁን በኋላ በ13 ብር እንዲሸጥ ተወስኗል። ይህ የ2 ብር ቅናሽ የደረገበት የዋጋ ማስተካከያ ምርታቸውን በነፃ ገበያ ውድድር ሲሸጡ በቆዩ የግል ዳቦ ቤቶች ላይ ብቻ የሚተገበር መሆኑ ተመልክቷል። በሌላ በኩል በመንግስት ድጎማና ድጋፍ የሚሰሩ የዳቦ ማምረቻዎች ዋጋ ላይ ምንም አይነት ለውጥ የሌለ ሲሆን፡ * የሸገር ዳቦ፡ በ5 ብር ከ50 ሳንቲም፤ * የብርሃን ዳቦ፡ በ5 ብር፤ * በመንግስትና በግል አጋርነት የሚሰሩ 29 የዳቦ ፋብሪካዎች፡ በ8 ብር ማሰራጨታቸውን በተለመደው ዋጋቸው ይቀጥላሉ።