← All news
News Oct 29, 2026 · 10d ago

ኒውክሊየር ኃይል ጨምሮ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ  ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውን  ተናግረዋል፡፡ ውይይታቸው በኒውክሊየር ኃይል፣ በጤናና ንግድ ዘርፎች ያለውን ትብብር እንዲሁም በጋራ ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮችን ያካተተ እንደነበረም ገልጸዋል። በተጨማሪም፣ ለውይይት፣ ለጋራ መግባባት እና ለኢትዮጵያ-ሩሲያ ግንኙነት ቀጣይነት ያለው እድገት ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነውም ተብሏል፡፡ አሐዱ ሬዲዮ