← All news
News Oct 29, 2026 · 10d ago

ዓመታዊ ግብርን ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ማሳወቅና መክፈል የሚያስችል አዲስ አሰራር ተዘረጋ

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ እንዳስታወቀው፣ ከእንግዲህ የደረጃ «ሀ» ግብር ከፋዮች ወደ ገቢዎች ቢሮ በአካል በመመላለስ የሚደርስባቸው እንግልትና ወረፋ አብቅቶለታል። ግብር ከፋዮች ባሉበት የንግድ ቦታ ሆነው የሂሳብ መዝገቦቻቸውን በኦንላይን በመላክ ክፍያቸውን በቀላሉ መፈጸም ይችላሉ።   አዲሱ አሰራር እንግልትን ከመቀነሱም በላይ፣ ከዚህ ቀደም ከእቁብ፣ ከብድር፣ ከውርስ እና ከስጦታ ገንዘቦች ጋር ተያይዞ ይነሱ የነበሩ የኦዲት ቅሬታዎችን በፍትሃዊነት የሚፈታ መሆኑ ተገልጿል።   "ቢሮው አክሎም፤ የደረጃ «ሀ» ግብር ከፋዮች ያለቅጣት ግብራችሁን አሳውቃችሁ ለመክፈል የተሰጠው የጊዜ ገደብ ጥቅምት 30 የሚያበቃ በመሆኑ፣ የሂሳብ መዝገባችሁን በኦንላይን፣ ተጨማሪ ሰነዶችን ደግሞ በኢሜይል በመላክ ክፍያችሁን እንድትፈጽሙ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።"