← All news
News Oct 29, 2026 · 10d ago

አቶ እስክንድር ነጋ ራሳቸውን ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ አመራርነት እና አባልነት  ማግለላቸውን አስታወቁ!

ፖለቲከኛው እስክንድር ነጋ ራሳቸውን ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ አመራርነት እና አባልነት  ማግለላቸውን ገልጸዋል።«ለከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ፖሊት ቢሮና ሥራ አስፈጻሚ » በሚል ርዕስ ለዶቼ ቬለ  በላኩት መግለጫ የዐማራ ሕዝብ ትግል "ትብብር ለህውልና" በሚባል አደረጃጀት እንደተጠለፈ አብራርተዋል። በድምጽ እና በጽሁፍ በቀረበው ደብዳቤው በዚህ ቡድን ሴራ አፋብን "ትብብር ለህውልና" የተባለው ሕወሓት ስሪት ስብስብ ውስጥ ገብቷል ያሉት አቶ እስክንድር፤ "ትብብሩ" ሕወሓት በ2013 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ሲቃረብ "የፌድራል ኃይሎች" በሚል መጠሪያ ያቋቋመው የትሮይ ፈረሱ እንጂ አዲስ ተቋም አይደለም በማለት ወቅሰዋል። «"ትብብሩ" ያኔም ዛሬም ፀረ-አማራ እና ፀረ-ኢትዮጵያ ነው በማለት ራቸውን ከአባልነት ጭምር ስላገለሉበት ሂደት አብራርተዋል። ከ"ትብብሩ" ሰባት ድርጅት መካከል አፋብን አንድ ድምፅ ብቻ ይዞ በፖለቲካ ሊለውጠውም ሆነ ሊመራው እንደማይችል እና ሕወሓት በ"ትብብሩ"ውስጥ ያለውን ወታደራዊ በላይነት መቼም ቢሆን አሳልፎ እንደማይሰጥ ለማወቅ ሊቅነትን አይጠይቅም» በማለትም ነው የገለጹት። በመጨረሻም አቶ እስክንድር  «በድርጅታችን ህገ ደንብ መሠረት ከአፋብን አባልነት እንድለቅ ይፈቀድልኝ ዘንድ በትህትና እጠይቃለሁ።» ብለዋል።አቶ እስክንድር ነጋ ከአማራ ፋኖ የትጥቅ ትግልን ከተቀላቀሉ በኋላ` በኋላ በተለያዩ ያለፉትን ጥቂት አመታት በተለያዩ አደረጃጀቶች ውስጥ በአመራርነት ጭምር ተሳታፊ ሲሆኑ መቆየታቸው ይታወሳል።