«በአርሲ የቀብር ሥርዓት ያከናወኑና የተጎዱትን ያከሙ ከ50 በላይ ነዋሪዎች መታሰራቸው ተገለጸ»
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በታጣቂዎች በተፈጸመው ጥቃት ለተገደሉ ንጹሐን ዜጎች የቀብር ሥርዓት የፈጸሙ፣ ሬሳ ያነሱ እንዲሁም የተጎዱ ሰዎችን ለማከም ሲሯሯጡ የነበሩ ከ50 በላይ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰማ። በጉዳዩ ላይ የተናገሩ አካላት፤ የታሰሩት አብዛኞቹ የሟቾች ቤተሰቦችና ዘመዶች መሆናቸውን ጠቁመው፤ እስሩ የተፈጸመው «ለቅሶ ሄዳችሁ» እና «እገዛ አድርጋችኋል» በሚል ምክንያት እንደሆነ በመግለጽ ሂደቱን አጣጥለውታል። @Seledadotio