ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማእከል የ1ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደረገ
ለማእከሉ የ1 ሚሊየን ብር ድጋፍ ያደረገው ተመራጭ የብድርና ቁጠባ ማኅበር ነው። ተቋሙ ድጋፍ ሲያደርግ ይሄ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ይሄኛው ድጋፍ የተደረገውም የምስረታ በዓላቸውን በማስመልከት እንደሆነ ለብስራት ሬዲዮ የተናገሩት በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ህሩይ ዓሊ ናቸው።የማህበሩ ድጋፍ ማዕከሉ ለሚያገለግላቸው ሕፃናትና ቤተሰቦች ያለውን ጥልቅ አጋርነትና ቁርጠኝነት ያሳየበት ነው ብለዋል። ዋና ሥራ አስፈጻሚው በሰጡት አስተያየት፦ «ተመራጭ የብድርና ቁጠባ ማኅበር እና አባላቱ በድጋሚ ለማእከሉ ድጋፍ በማድረጋቸው እንዲሁም የድጋፍ መጠናቸውን ከ100ሺ ብር ወደ 1ሚሊዮን ብር በማሳደጋቸው አመስግነዋል።እንደዚህ ዓይነት ስጦታዎች ቤተሰቦቻቸው የሕክምና ወጪያቸውን መሸፈን ባለመቻላቸው ምክኒያት ለዓመታት ሕክምናቸውን በመጠባበቅ ላይ የሚያሳልፉ ሕፃናትን በቀጥታ ለማከም የሚውል መሆኑን ገልፀዋል። በተጨማሪም ይህ ድጋፍ በማኅበረሰባችን ውስጥ የሚገኙ ተቋማት የጀመርነውን ሥራ የሚደግፉና የሚያበረታቱ መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ፣ ሌሎችም የእነሱን አርዓያ ይከተላሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን ሲሉ አቶ ህሩይ ጨምረው ተናግረዋል ። Dagu