← All news
News Oct 28, 2026 · 10d ago

​«በኦሮሚያ ክልል በክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እንዲቆሙ ጥሪ ቀረበ»

​የአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ አብላጫ አባላት፤ በኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ላይ እየተፈጸሙ ያሉ ጥቃቶች «ፈጽሞ ተቀባይነት የላቸውም» በማለት አውግዘዋል። ​ኮሚቴው በኤክስ (Twitter) ገጹ ባወጣው መግለጫ፤ የሃይማኖት ማኅበረሰቦች ከጥቃት እንዲጠበቁ እና ወንጀለኞች ተጠያቂ እንዲሆኑ የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ አሳስቧል።