በአሜሪካ እና እስራኤል ላይ የተቃጣ ማስጠንቀቂያ፤ ኢራን ከመሬት ስር የተደበቁ በርካታ የሻሂድ ድሮኖቿን የሚያሳይ ምስል ይፋ አደረገች
ኢራን ከመሬት ስር በተገነባ ሚስጥራዊ የጦር ካምፕ ውስጥ በብዛት የተከማቹ ሻሂድ-አይነት (Shahed-style) አጥቂ ድሮኖችን የሚያሳይ አዲስ ተንቀሳቃሽ ምስል ይፋ አደረገች። ይህ እርምጃ ዋሽንግተን እና ቴል አቪቭ ላይ የተቃጣ የተዘዋዋሪ ማስጠንቀቂያ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን፣ ኢራን የአየር ጥቃት ቢሰነዘርባት እንኳ የአየር ኃይል አቅሟ የማይደናቀፍና ለአጸፋ ምላሽ ዝግጁ መሆኑን ለማሳየት ያለመ ነው ተብሏል። ቴህራን በዚሁ እርምጃዋ የወታደራዊ ዝግጁነቷን ጥንካሬ የምታሳይበትና ለረጅም ጊዜ ሊዘልቅ የሚችል ግጭት የስነ-ልቦና ዝግጅት ማድረጓን ጠቁማለች። ሆኖም ይፋ የተደረገው ምስል የቦታውን ትክክለኛ መገኛ፣ ቪዲዮው የተቀረጸበትን ጊዜ እንዲሁም ኢራን በአሁኑ ወቅት በአገልግሎት ላይ የዋሉ ድሮኖች ብዛት በገለልተኛ አካል ለማረጋገጥ አልተቻለም።