በትግራይ መደባይ ጠረር ጤና ጣቢያ ከጥቃት በመሸሽ ላይ የነበሩ ወላጆች እና ከአራት ልጆቹ ጋር የነበረ አባት በድሮን ጥቃት ተገደሉ።
በሰሜን ምዕራብ ትግራይ በታሕታይ ቆራሮ ወረዳ መደባይ ጠረር በተባለ ስፍራ ጥቅምት 9 እና 21 ቀን በተፈጸሙ ሁለት የድሮን ጥቃቶች የስምንት ዓመት ልጅን ጨምሮ ሰባት ሲቪል ዜጎች ሲገደሉ፣ ሌሎች ስድስት ሰዎች መቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ። የመጀመሪያው ጥቃት ጥቅምት 2 ቀን እኩለ ቀን በመደባይ ጠረር ክሊኒክ ላይ የተፈጸመ ሲሆን፣ በዚህም ምክንያት ሁለት ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች አራት ደግሞ መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የጥቃቱ ሰለባ የሆኑት ምጥ የያዛትን ሴት ልጃቸውን ይዘው ወደ ክሊኒክ ያመሩ እናትና አባት ናቸው ሲሉ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ሁለተኛው ጥቃት በጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ገደማ በተመሳሳይ አካባቢ የቤተሰብ አባላት ተሰብስበው በነበሩበት አንድ መኖሪያ ቤት ላይ ያነጣጠረ ነው። ጥቃቱ አባትን እና የአንዲት ስምንት ዓመት ሕፃን ልጅን ጨምሮ አራት ልጆቻቸውን በአጠቃላይ አምስት ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈ ሲሆን፣ ሁለት የቤተሰብ አባላትን አቁስሏል።