← All news
News Oct 27, 2026 · 11d ago

«የተማረከው ጄኔራል ጆን ሜዲድ፡ “ከእንግዲህ ጆን ሜዲድ አትበሉኝ”»

​የጦርነቱ ፍጻሜና መማረክ፦ «እንጨርሰዋለን» ሲባል የነበረው ጦርነት ተጠናቆ በአሁኑ ወቅት መማረኩን አስመልክቶ ለቀረበለት ጥያቄ የተሰጠው ምላሽ፤ «ቃሌን አላፈረስኩም፤ እስከ መጨረሻው ቆሜ ነበር፤ ጥይቶችና ሰዎች ሲያልቁብኝ የሰላም ስትራቴጂካዊ ማስተካከያ አድርጌያለሁ» ሲል ገልጿል። ​ስልጣን፣ ሀብት እና የራያ ጉዳይ፦ ሚሊየነር መሆኑና በባንክ ውስጥ ገንዘብ እንዳለው እየታወቀ በራያ ውስጥ ለቡድኑ የዞን ስልጣን ለመስጠት ንጹሐን ዜጎች እና የተፈናቀሉ ሰዎች መገደላቸው ለተነሳበት ጥያቄ፤ «ገንዘብ ከሞት ለማዳን ይረዳሃል፤ የራያ ህዝብ እንዳይመረር ልጆቹን ለማስተካከያ ኃይል ለመጠቀም ሞክሬያለሁ፤ የተሳሳተ ከሆነ ከተፈታሁ በኋላ በመጽሐፌ ምዕራፍ 12 አካትቼዋለሁ» ብሏል። ​የተማረ መደብና አዲስ ስም፦ «ማይክሮፎን ከድሮኖች አያድኑም፤ ሰዎች ቢጠሉህ ማሸነፍ እንደማትችል እና ዋናው ጥበብ በሕይወት መቆየት እንደሆነ ተምሬያለሁ» ያለው የጦር መሪው፤ ከእንግዲህ ወዲያ ጆን ሜዲድ ተብሎ መጥራት እንደማይፈልግ ገልጾ፤ «ጆን ቤርድ ወይም ጆን ኪውዲድ ብላችሁ ጥሩኝ» በማለት ሌሎችም ሕይወታቸውን እንዲያድኑ ጥሪ አቅርቧል። ​@Seledadotio