በሩሲያ አንዳንድ ወጣቶች ቆንጆ ለመሆን ፊታቸውን በመዶሻ በመምታት ለማስተካከል ሲሞክሩ እየተጎዱ ነው
በሩሲያ ከ15 እስከ 45 ዓመት የሆኑ ወንዶች ይበልጥ ማራኪ እና ወንድነት ያለው ገጽታ ለማግኘት ሲሉ "ቦን ስማሺንግ" በመባል የሚታወቀውን አደገኛ ተግባር እየፈጸሙ ነው። በዚህም ጉንጫቸውን እና አገራቸውን በመዶሻ በመምታት የአጥንት እድገት ለማበረታታት ይሞክራሉ። እስካሁን ከእነዚህ ወጣቶች መካከል ከመቶ በላይ የሚሆኑት ከባድ ጉዳቶች አጋጥሟቸዋል ሲሉ ሰሞኑ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ከጉዳቶቹም መካከል የደም መፍሰስ እና የከባድ አገጭ ስንጥቆች፣ የነርቭ ጉዳት እና ዘላቂ የቲሹ መጎዳትን እያስተናገዱ ይገኛሉ። የሕክምና ባለሙያዎች እንደሚሉት ይህ ድርጊት የሚጠበቀውን ውበት በፍጹም አያመጣም፤ ይልቁንስ ዘላቂ ጠባሳዎችን በማስከተል በቀዶ ሕክምና ጭምር እንዲታከሙ የሚያደርግ አደገኛ ድርጊት ነው።