የሜ/ጄ ዮሃንስ (ጆን መዲድ) የትጥቅ ትግል መጨረሻ ምርኮ ሆነ፤ የህወሓት አመራሮች ፍፃሜ አላማረም
የህወሓት አመራር አባል እና ሜ/ጄ ዮሃንስ (ጆን መዲድ) ከትጥቅ ትግል ጋር የተያያዘው የረጅም ዓመታት ጉዞ በመጨረሻ በምርኮ ተጠናቋል። ከዚህ በፊት በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሄዱ የተለያዩ ግጭቶች ውስጥ የነበረው ትልቅ ሚና እና በህወሓት የአመራር መዋቅር ውስጥ የነበረው ከፍተኛ ተሳትፎ በመጨረሻም ከተደበቀበት ቦታ በቁጥጥር ስር ከመዋል አላዳናቸውም። ሜ/ጄ ዮሃንስ በህወሓት የትጥቅ ትግል ዘመን ከወታደራዊ አመራሩ ጋር ተያይዞ የቆዩ ሲሆን፣ በኋላም በትግራይ የተካሄዱ የጦርነት ዙሮች ውስጥ ተሳትፎ እንደነበራቸው የሚታወቅ ነው።ዛሬ የሰተማው የምርኮ ዜና ደግሞ የህወሓት ወታደራዊ አመራሮች በትጥቅ ግጭት የተከተሉት መንገድ ወዴት እንደደረሰ የሚያሳይ ክስተት ሆኗል።