በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ጥቅምት 10 እና 14 በመርቲ እና ሸርካ ወረዳ 60 ምእመናን እንደተገደሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ አስታወቀ።
በመርቲ ወረዳ አንጋዳ ቀበሌ 14 ምእመናን እንዲሁም በሸርካ ወረዳ ጠሬታ ጮሌ ቢርቦ 46 ምእመናን በጭካኔ መገደላቸውን ሲኖዶሱ ገልጧል። ከ20 በላይ ወገኖች ከባድ የመቁሠል አደጋ ደርሶባቸው ሆስፒታል ይገኛሉ ተብሏል። ድርጊቱ አስነዋሪ፣ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣ የሃይማኖት ነፃነትና በሕይወት የመኖር ሕገ መንግሥታዊ መብትን የጣሠና ከሃይማኖትም ሆነ ከተፈጥሮ ሕገ ሰብዕና የወጣ መሆኑን በመግለጽ ሲኖዶሱ ግድያውን አውግዟል። @Seledadotio