← All news
News Oct 26, 2026 · 13d ago

የዶናልድ ትራምፕ አወዛጋቢ ንግግር፡ ሶማሊያ “በዓለም ላይ ለመኖር አስቸጋሪ ሀገር ናት”

​ዶናልድ ትራምፕ በሰጡት  ጠንካራ አስተያየት ሶማሊያን “በዓለም ላይ ለመኖር ከባዱ ሀገር ናት” በማለታቸው፣ መንግሥት እንደሌላትና በባህር ላይ ጥቃቶችን እንደምትፈጽም በመወንጀል ከፍተኛ ትችት ሰነዘሩ። ​በንግግራቸው ወቅት ሀገሪቱ ፖሊስም ሆነ አስተዳደር እንደሌላትና ሕዝቡ እርስ በእርሱ እንደሚጋደል ገልጸዋል። የትራምፕ ይህ አስተያየት ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ትኩረት የሳበ ሲሆን፣ በሶማሊያ ወቅታዊ ፖለቲካዊና ጸጥታ ሁኔታ ላይ ሰፊ ክርክር አስነሷል። ​በባህር ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እና የባህር ላይ ወንበዴዎች ጉዳይ አሳሳቢ መሆኑ ተነስቷል። በንግራቸው ​ የሀገሪቱን ተቋማት መዳከም እና የሕግ አስከባሪዎች እጥረት መኖሩ ተመላክቷል። ​ንግግሩ በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች እና በስደተኞች ዙሪያ ከፍተኛ ውይይት ፈጥሯል።