← All news
News Oct 26, 2026 · 13d ago

የብሪታንያዊው ድንቅ ህክምና፡ ከክንድ ቆዳ የተሰራ አዲስ የወንድ ብልት

​በብሪታንያ የሚኖር አንድ ሰው በብልት ካንሰር ተይዞ ህክምና በማድረጉ አዲስ ህይወት አግኝቷል። በ2022 በብልቱ ላይ እብጠትና ህመም ያስተዋለው ግለሰቡ፣ ካንሰር እንደያዘው በመረጋገጡ የተነሳ የብልቱ ክፍል ሙሉ በሙሉ እንዲወገድ ተደርጓል። ​ዶክተሮች ከግራ ክንዱ ላይ ቆዳ፣ የደም ስሮች፣  ደም ወሳጅ ቧንቧ እና ነርቮች በመውሰድ አዲስ ብልት ሰርተውለታል። ቀዶ ጥገናው የተሳካ ሲሆን፣ አዲሱ አካል ስራውን በብቃት ማከናወን መጀመሩ ተገልጿል። ​ የተጎዳው አካል ሙሉ በሙሉ በመወገዱ ከክንድ ቲሹ አዲስ ተገንብቷል። ​አዲሱ ብልት ስራውን የጀመረ ሲሆን፣ የታካሚው ህይወት ወደ ቀድሞው ተመልሷል። ​ አሁንም የብልት ጆሮ ማስተካከል እና ለግንኙነት የሚያስችል ተከላ ማድረግ ይቀራል። ​ይህ አስደናቂ የህክምና ስኬት በህክምናው ዓለም ትልቅ ትኩረትን ስቧል።