የአየር መንገዳችን የብራንድ ዋጋ323.9 ሚ. ዶላር መድረሱ ተገለጸ
በአዲስ የፈረንጆች ዓመት የኩባንያዎች ዋጋ ግምገማ መሠረት የኩራት ምንጭ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የምርት ስያሜ (Brand Value) ዋጋ 323.9 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር መድረሱን የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘገቡ። የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን የዓለም አቀፉን አእምሯዊ ንብረት ድርጅት (WIPO) ዋቢ በማድረግ እንደገለጸው፤ በሀገሪቱ ከፍተኛ የምርት ስያሜ ዋጋ ካላቸው ከ5 ሺህ በላይ ኩባንያዎች መካከል ብሔራዊ አየር መንገዳችን አንደኛ ደረጃን በመያዝ አዲስ ታሪክ ጽፏል። ይህ አስደናቂ ስኬት አየር መንገዱ በዓለም አቀፍ ገበያ ያለው ተወዳዳሪነት እያደገ መጣቱን በሰፊው የሚያሳይ ነው።