በኦሮሚያ ክልል ሽርካ ወረዳ በሳምንት ልዩነት ውስጥ በተፈጸመ አዲስ ጥቃት ቢያንስ አምስት ሕጻናትን ጨምሮ ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸው ሦስት የዐይን እማኞች ለቢቢሲ ተናገሩ። ትናንት ቅዳሜ ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም. በተፈጸመው ጥቃት የተገደሉ "46 ሰዎች" በአካባቢው በሚገኘው ቤተ ክርስቲያን "በአንድ ጉድጓድ" መቀበራቸውን ሁለት ነዋሪዎች፣ ቀብሩ የተፈጸመበት ቤተ ክርስቲያን እና የወረዳው የቤተ ክርስቲያን ምንጮች ገልጸዋል።