← All news
News Oct 25, 2026 · 13d ago

"ለሕወሓት አምስተኛ እድል አንሰጠውም" ፊ/ማርሻሉ

በዛሬው ዕለት በተከበረው የመከላከያ ቀን ላይ የተገኙት  ፊልድ ማርሻል ብርሐኑ ጁላ ሕወሓትን በተመለከተ አስተያየት ሰጥተዋል። ከዚህ ቀደም ለሕወሓት የተሰጡ አራት እድሎች እንደነበሩ በመግለፅ አምስተኛ እድል አንሰጠውም ብለዋል። ሕወሓት ለአራተኛ ጊዜ በቅርቡ የከፈተው ጦርነት መቀልበሱን እና የሕወሓት አመራሮች ወደ ወደ ኤርትራ መንደፈራ መሸሸጋቸውንም ገልፀዋል። ሰባት የሀገር ውስጥ ታጣቂዎችን እና ሶስት ጣልቃ ገብ የውጪ ሀገራትን መከላከያ ሰራዊት አሸንፏል ብለዋል። መከላከያ ያፈርሳል እንጂ አይፈርስም ሲሉም ተደምጠዋል።