ቱርክ በ5 ዓመት ውስጥ 5 ሚሊዮን
ድሮኖችን ለማምረት አቅዳለች ቱርክ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ውስጥ 5 ሚሊዮን፣ በ10 ዓመታት ውስጥ ደግሞ እስከ 10 ሚሊዮን የሚደርሱ ድሮኖችን ለማምረት ማቀዷን የሀገሪቱ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሴልቹክ ባይራክታሮግሉ ገለጹ። ይህ ዕቅድ ቱርክ የወታደራዊ ድሮን ምርቷንና የቴክኖሎጂ አቅሟን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ እያደረገች ያለውን ትልቅ እንቅስቃሴ ያሳያል። በቅርቡ በተደረገ የባህር ኃይል ልምምድ ላይ ቱርክ ሰው ያላቸውንና ሰው አልባ የጦር መሣሪያዎችን አጣጥማ የመጠቀም አቅሟን አሳይታለች። በዚህ የቀጥታ ተኩስ ልምምድ ላይ ካልካን የተባሉ ድሮኖች፣ ኤፍፒቪ ድሮኖች እና ፒራና የተባሉ ሰው አልባ የባህር ላይ ተኳሽ ጀልባዎች ሥራ ላይ ውለዋል። እንደ ኤታማዦር ሹሙ ማብራሪያ፣ በቀጥታ ወደ ላይ መነሳትና ወደ ታች ማረፍ የሚችሉ ሰው አልባ ድሮኖች እና ሰው አልባ የውሃ ውስጥ መሣሪያዎች ለቱርክ የባህር ኃይል የወደፊት አቅም በጣም አስፈላጊ ናቸው። በተጨማሪም ሀገሪቱ የጦር መርከቦችን በሀገር ውስጥ የማምረትና የማደስ ሙሉ አቅም እንዳላት ገልጸዋል።