← All news
News Oct 24, 2026 · 14d ago

የትግራይ ሰላም ኃይል ለህወሓት ካድሬዎች የምክክር ምዝገባ ጥሪ አቀረበ

የትግራይ ሰላም ኃይል (TPF) ለህወሓት ካድሬዎች ከጥቅምት 15 እስከ 19 ቀን 2019 ዓ.ም. በአቅራቢያቸው ባለ የፖሊስ ጣቢያ በመቅረብ ለምክክር እንዲመዘገቡ ጥሪ ማቅረቡ ተገልጿል። በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ የማይመዘገቡ ካድሬዎች፣ ከህወሓት ጋር በመቀጠል ለመሥራት እንደመረጡ እንደሚቆጠሩ በመግለጫው መጠቀሱ ተነግሯል። የምክክርና የመመለስ ጥሪው በትግራይ ለተፈጸሙ ኢፍትሐዊ ድርጊቶች ዋነኛ መሣሪያ ሆነው አገልግለዋል ለተባሉ የህወሓት ካድሬዎች የቀረበ ዕድል መሆኑ ተገልጿል።