← All news
News Oct 24, 2026 · 14d ago

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሞዛምቢኩ ፕሬዚዳንት ጋር በጋራ ጥቅም ጉዳዮች ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 12ኛው የጣና ከፍተኛ ደረጃ የአፍሪካ ደህንነት ፎረም ከመጀመሩ አስቀድሞ የሞዛምቢኩን ፕሬዚዳንት ዳንኤል ቻፖን በባሕር ዳር በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተቀብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው የሞዛምቢኩን ፕሬዚዳንት በደስታ መቀበላቸውን ገልጸው፣ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከርና የጋራ ጥቅሞችን ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የሁለትዮሽ ውይይት ማካሄዳቸውን አስታውቀዋል። የሞዛምቢኩ ፕሬዚዳንት ዳንኤል ቻፖ በ12ኛው የጣና ከፍተኛ ደረጃ የአፍሪካ ደህንነት ፎረም ላይ ለመሳተፍ ባሕር ዳር የገቡ ሲሆን፣ በጉብኝታቸው ወቅት ከኢትዮጵያ አመራሮች ጋር በጋራ ጥቅም ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ተገልጿል።