← All news
News Oct 23, 2026 · 15d ago

«እንግሊዝ በሰሜን ኢትዮጵያ በድርቅና በግጭት ለተጎዱ ወገኖች የ8 ሚሊዮን ፓውንድ የሰብአዊ እርዳታ አደረገች»

​የእርዳታ ድጋፍ መጠን፦ የእንግሊዝ መንግሥት በሰሜን ኢትዮጵያ በድርቅ እና በግጭት ለተጎዱ ነዋሪዎች የሚውል የ8 ሚሊዮን ፓውንድ የሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል። ​የእርዳታ አከፋፋይ ድርጅቶች፦ ይህ የገንዘብ ድጋፍ በዓለም አቀፉ የረድኤት ኮሚቴ (IRC) እና በዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) በኩል ለተጎጂዎች እንደሚሰራጭ ተመላክቷል። ​የድጋፉ ዓላማ፦ የተመደበው በጀት አስቸኳይ የነፍስ አድን የገንዘብ ድጋፎችን እና አስፈላጊ የሕክምና ቁሳቁሶችን እጅግ ለተጎዱ ወገኖች ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል። ​@Seledadotio