← All news
News Oct 23, 2026 · 15d ago

በራያ አላማጣ ከተማ ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ መቀሰቀሱና ተኩስ መከፈቱ ተሰማ‼️

እንደ ምንጮች ዘገባ ከሆነ፣ የተቃውሞ ሰልፉ የተቀሰቀሰው በአካባቢው እየተካሄደ ነው የተባለውን አስተዳደራዊ እና ምርጫ ነክ እንቅስቃሴዎችን በመቃወም ነው። በሰልፉ ላይ የተሳተፉ ወጣቶች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ አደባባይ በመውጣት «እኛ አማራ ነን»፣ «በኃይል አንገዛም» እና «የትግራይ ሰላም ኃይል አካባቢውን ለቆ ይውጣ» የሚሉ መፈክሮችን ሲያሰሙ እንደነበር ተገልጿል። ተቃውሞውን ለመበተን በቦታው በሚገኙ የጸጥታ ኃይሎች በኩል የተኩስ ድምፅ መደመጡ የተገለጸ ሲሆን፣ በዚህም ምክንያት የህዝብ ተቃውሞው በኃይል እንዲበተን መደረጉ ታውቋል።