← All news
News Oct 23, 2026 · 15d ago

ወደ መቐለ ሲጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ ባስ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 3 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በአዳማ ከተማ መግቢያ በሕዝብ ማመላለሻ ባስ እና ተሳቢ መኪና መካከል በተፈጠረ (ግጭት) የትራፊክ አደጋ የአውቶቡሱ ሹፌርና ረዳትን ጨምሮ ሦስት ሰዎች ወዲያውኑ ህይወታቸውን እንዳጡ አንድ ተሳፋሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። " አደጋው ከጠዋቱ 12፡15 አካባቢ ነው የደረሰው " ያለው በባሱ ውስጥ የነበረ ተሳፋሪ " 3 ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ ፣ የተጎዱት ሰዎች ለሕክምና ወደ ሕክምና ማዕከላት ተወስደዋል " ብሏል። " ተሽከርካሪው ከፍተኛ የሆነ ፍጥነት ላይ ነበር ፤ የአደጋውን መንስኤ ለማጣራትም የትራፊክ ፖሊሶች ወደ አደጋው ቦታ ደርሰዋል " ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ተናግሯል።