← All news
News Oct 23, 2026 · 15d ago

ሰሞነኛው ጉንፋን‼️

በአዲስ አበባ ከተማ ሰሞኑን ከወትሮው የተለየ የጉንፋን ዓይነት አለመከሰቱን የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ አስታወቀ‼️   👉ወቅቱ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት የተመለሱበት በመሆኑ ምክንያት ከትምህርት ቤቶች በመነሳት ወደ ቤተሰብ የተሰራጨ የጉንፋን ሕመም እንጂ፣ ከዚህ ቀደም ከነበሩት ለየት ያለ አለመሆኑን የቢሮው ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ ገልጸዋል።   👉ሰሞኑን በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ለየት ያለ ዓይነት የጉንፋን ሕመም በመዲናዋ ተስተውሏል ማለታቸውን ተከትሎ ኃላፊው በሰጡት ምላሽ፤ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ወቅት ይከሰት ከነበረው ሁኔታ ጋር ሲነጻጸር ዘንድሮ የጉንፋን ሕመም ስርጭት መቀነሱን አስረድተዋል።   👉አዲስ አበባ ከሀገር ውስጥና ከውጭ የሚመጡ እንግዶች የሚያርፉባትና የሚተላለፉባት ትልቅ የእንቅስቃሴ ማዕከል እንደመሆኗ፤ ሊከሰቱ የሚችሉና ከውጭ ሊገቡ የሚችሉ ተላላፊ በሽታዎችን ለመቆጣጠር አሁን ላይ በርካታ ስፍራዎች ውብና ጽዱ ሆነው መልማታቸው ከፍተኛ እገዛ ማድረጉን ጠቁመዋል። በዚህም የተላላፊ በሽታዎች መጠን መቀነሱንና ከውጭ ሊገቡ የሚችሉ በሽታዎች ላይም ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።   👉በተጨማሪም ቢሮው ነዋሪዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን በማድረግ እንዲሁም አጫጭር መንገዶችን በእግር በመጓዝ አእምሯዊና አካላዊ ጤናቸውን እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርቧል።