← All news
News Oct 23, 2026 · 16d ago

የተሟላ የሂሳብ መዝገብ ለማያቀርቡ የይዘት ፈጣሪዎች ከጠቅላላ ገቢያቸው ላይ 15 በመቶ ተቀናሽ ይደረጋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የ2018 የግብር ዓመት የታክስ ሂሳብ መግለጫዎች ግብርን ለማሳወቅ ሲቀርቡ የግብርና ታክስ አሰባሰብ ሂደቱን ይበልጥ ውጤታማ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ ለማድረግ የሚያስችል የዴስክ ኦዲት (Desk Audit) ማስፈጸሚያ(Guideline) ማዘጋጀቱን አስታውቋል። ​ቢሮው ባወጣው ሰነድ ፣ በተለይም የደረጃ «ሀ» ግብር ከፋዮች የሚያቀርቧቸውን የሂሳብ መዛግብት በጥራትና በፍትሐዊነት ለመመርመር እንዲሁም ባለፉት ዓመታት የታዩ ክፍተቶችን ለማረም ማስፈጸሚያው ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብሏል።  በማስፈጸሚያ ሰነዱ ውስጥ ከተካተቱ ነጥቦች መካከል በባንክ ሂሳባቸው የሚታየውን ያልተገለጸ ከፍተኛ ገንዘብ "የእቁብ ነው" በማለት ምክንያት ለሚያቀርቡ ግለሰብ ግብር ከፋዮች ጥብቅ ማስረጃ አስገዳጅ ማድረግ አንዱ ነው። ግብር ከፋዮቹ :- - የእቁብ ሰብሳቢና ዳኛ የተፈረመበት ማስረጃ፣ - የእቁብተኞች ዝርዝር፣ - የእቁብ ደብተር፣ እንዲሁም እቁቡ በዕጣ ወይም በግዢ መገኘቱን የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ ካልቻሉ ገንዘቡ እንደ ንግድ ገቢ ተቆጥሮ ግብር ይጣልበታል። የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች በማህበራዊ ሚዲያ (ዩቲዩብ፣ ቲክቶክ፣ ቴሌግራም) ከሚያገኙት ማስታወቂያና ስፖንሰርሺፕ በተጨማሪ፣ ከተከታዮች በቀጥታ ሥርጭት (Live streaming) ወቅት የሚሰጡ ስጦታዎችና ስታሮች (Gifts/Stars)፣ የብዙሃን የገንዘብ ድጋፍ (Crowdfunding) እና የደንበኝነት ክፍያዎች (Membership Fees) ግብር እንደሚከፈልባቸው ተመላክቷል።