"አባቴ በሕይወትና በሙሉ ጤንነት ላይ ይገኛል"
አንጋፋው ድምጻዊ መሀሙድ አህመድ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው ወሬ ሙሉ በሙሉ ሐሰት መሆኑን ልጁ ሀብቱ መሀሙድ ገለጸ። ልጁ ሀብቱ ባስተላለፈው መልዕክት፣ አባቱ በሕይወትና በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ አረጋግጧል። አክሎም፣ አባቴ በሕይወት እያለ የሞት ወሬ ማሰራጨት እጅግ አስነዋሪ ድርጊት ነው ሲል ገልጾ፣ ህዝቡ የሐሰት መረጃ የሚያሰራጩ ገጾችን ሪፖርት በማድረግ እንዲያስወግዳቸው ጥሪ አቅርቧል። ድምጻዊ መሀሙድ አህመድ በቅርቡ ጥቅምት 11 ቀን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል በተካሄደ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ በክብር እንግድነት ተገኝቶ እንደነበር ይታወቃል።