← All news
News Oct 22, 2026 · 16d ago

“ሰላም አግኝተናል፣ የወደሙ ተቋማትን እንገነባለን” - የመቐለ ከተማ ከንቲባ

በመቐለ ከተማ የወደሙ የአገልግሎት ተቋማትን ፈጥኖ ወደ ሥራ ለማስገባትና አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍን ለማድረስ ሰፊ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የመቐለ ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ሽሻይ አማረ ገለጹ። ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታም በፌዴራል መንግሥት በተከናወነው የሰላም ማስከበር ሥራ የትግራይ ሕዝብ ከረጅም ጊዜ ውጥረት ወጥቶ ሰላምና እረፍት ማግኘቱን ተናግረዋል። ከንቲባው እንደገለጹት፣ ሕዝቡ ያገኘውን ሰላም እንዳያጣ ከባለአደራ አስተዳደሩ ጋር በመተባበር ሰላሙን ማጽናት ይገባል። በከተማዋ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ጣቢያዎችና ሆስፒታሎች ላይ ከፍተኛ ውድመትና ዝርፊያ መፈጸሙንም ጠቁመዋል። በተጨማሪም ለአስቸኳይ ድጋፍ የተጋለጡ ሕፃናትን፣ እናቶችንና አረጋውያንን ለመደገፍ የዕለት ደራሽ ምግብና ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎችን በፍጥነት ማድረስ ቀዳሚ ተግባር መሆኑን ከንቲባው አስምረውበታል። በቀጣይም የወደሙ ተቋማትን መልሶ በመገንባት የከተማዋን መደበኛ አገልግሎት ለማስመለስ እንደሚሠሩ ገልጸዋል።