← All news
News Oct 22, 2026 · 16d ago

የ #ኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት ምዘና ደረጃ አሁንም አሽቆለቆለ‼️

የአለም አቀፍ የፍትህ ፕሮጀክት (WJP) ይፋ ባደረገው የ2026 የሕግ የበላይነት መረጃ ጠቋሚ መሰረት፣ የኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት አፈጻጸም አሁንም ማሽቆልቆሉ ተመልክቷል። በዚህም መሠረት አገሪቱ ከ143 አገሮች መካከል 133ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። አዲሱ ግምገማ ሀገሪቱ ደረጃዋ ለበርካታ ዓመታት መሽቆልቆሉን መቀጠሉን ይፋ በማድረግ ከዓለም አቀፍ እና ከሰሃራ በታች ካሉ አፍሪካ አገሮች ደረጃ ግርጌ መቀመጧን አመላክቷል። ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም. ይፋ የሆነው የ2026 መረጃ ጠቋሚ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአምባገነንነት አዝማሚያ እየሰፋ መምጣቱን፣ በአስፈጻሚ አካል ላይ የሚደረጉ የቁጥጥር ገደቦች መዳከማቸውን፣ የዳኝነት ነፃነት መቀነሱን እና በመሠረታዊ ነፃነቶች ላይ የሚደረጉ ገደቦች በዓለም አቀፍ ደረጃ የሕግ የበላይነት እንዲሸረሸር አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆኑን የአለም አቀፍ የፍትህ ፕሮጀክት (WJP) ሲያስጠነቅቅ መቆየቱን ተከትሎ የወጣ ነው።