← All news
News Oct 22, 2026 · 16d ago

በሰሜን ወሎ ሳንቃ አካባቢ በመከላከያ ሠራዊትና በፋኖ መካከል ብርቱ ውጊያ መካሄዱ ተገለጸ»

​የውጊያው ኹኔታ፦ በደቡብ ወሎ ሳንቃ አካባቢ በመከላከያ ሠራዊትና በፋኖ መካከል ከአለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ብርቱ ውጊያ መካሄዱን የዓይን እማኞች ገልጸዋል። ​የመንገድ መዘጋት፦ በከተማዋ በነበረው ውጊያ ምክንያት ከወልድያ ወደ ባሕር ዳር የሚወስደው መንገድ ተዘግቶ የቆየ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን ለተሽከርካሪዎች ክፍት መሆኑ ተመላክቷል። ​የተባባሰ ውጥረት፦ በሰሜን ወሎ መርሳ እና በአካባቢው ከትናንት ጀምሮ ወታደራዊ ውጥረቱ መባባሱ ተሰምቷል።