← All news
News Oct 22, 2026 · 17d ago

የሚዋጥ የወሊድ መከላከያ  መድሀኒትን መጠቀም ለጡት ካንሰር ያጋልጣል ተባለ

የጡት ካንሰር በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ደረጃ  በአንደኝነት በተለይም የሴቶችን ህይወት እየቀጠፈ ያለ በሽታ ነው ፡፡ የጡት ካንሰር በአብዛኛው ሴቶችን የሚያጠቃ እንደሆነና በዋናነት የሚተላለፈው በቤተሰብ ከእናት ወደ ልጅ  ቢሆንም ሌላው ተጋላጭነትን የሚጨምሩ መንገዶች ሲጋራ ማጨስ፣ አልኮልን አዘውትሮ መጠቀም አለመውለድ እና  አለማጥባት እንደሆኑ ለብስራት ሬዲዮ የተነናገሩት በወራቤ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቤተሰብ ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ሔርሜላ አየለ  ናቸው፡፡ በተጨማሪም ለወሊድ መከላከያ ተብሎ የሚወሰደውን የሚዋጥ መድሀኒት መጠቀም እና ከእድሜ ጋር ተያይዞ ከ40 ዓመት በላይ መሆን ለበሽታው ተጋላጭ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡በሽታው በዋናነት ጎልቶ የሚታየው ከአርባ ዓመት በላይ ቢሆንም አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ስርጭቱ እየጨመረ በመምጣቱ ከ30 ዓመት ጀምሮ ላሉ ሴቶች የቅድመ ምርመራ እንዲያደርጉ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚስተዋለው ትልቁ ችግር ከረፈደ በኋላ ማለትም በሽታው ወደ ሌላ ሰውነት ክፍሎች ከተሰራጨ በኋላ እና  ሰውነታቸውም ተጎድቶ አቅም ከሳጣቸው በኋላ ወደ ህክምና ተቋማት መድረስ እንደሆነ የህክምና ባለሙያው ገልፀዋል፡፡ በሽታው ግን በጊዜ ከተደረሰበት እና ወደ ሳንባ፣ ወደ ጉበት፣ ወደ አጥንት እና ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ሳይሰራጭ እባጩን ባለበት ከተገኘ ቀዶጥገና ተሰርቶ እና የጨረር ህክምና ወስዶ የመዳን እድሉ 90 በመቶ እእደሆነ ተናግረዋል።   ለካንሰር ህክምና የሞኖግራፊ ምርመራ ተመራጭ አንደሆነ እና በተለያዩ ሀገራት ይህንን መሳሪያ ይጠቀማሉ፡፡ ነገር ግን በመካከለኛ እና በዝቅተኛ በሆኑ ሀገራት የአለም ጤና ድርጅት ባስቀመጠው መስፈርት አካላዊ የጡት ምርመራ በማድረግ ምርመራው እንደሚሰጥ አብራርተዋል።   በምርመራውም በጡት ውስጥ ከ2 ሴንቲሜትር ጀምሮ ያለ እባጭ ማግኘት ዶ/ር ሔርሜላ አየለ  ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡