የሕወሓት መሪዎች ከፍተኛ መጠን ያለው
መሣሪያ ይዘው ኤርትራ መግባታቸው ተነገረ ከፌዴራል መንግሥት ጋር ተባብሮ የሚሠራው የትግራይ ሰላም ኃይል አዛዥ እና የክልሉ ባለአደራ አስተዳደር የፀጥታና ሰላም ዋና አስፈጻሚ ብ/ጄ ገብረ እግዚአብሔር በየነ ኃይሉ፤ የሕወሓት መሪዎች ከፍተኛ መጠን ያለው የጦር መሣሪያና መድኃኒት ይዘው ወደ ኤርትራ ድንበር መሻገራቸውን ተናገሩ። መቐለ ከተማ ውስጥ ለነዋሪዎች ባሰሙት ንግግር ይህንን ይፋ ያደረጉት ጄኔራሉ፣ መሪዎቹ ወደ ኤርትራ ድንበር መሻገራቸውን ለአንድ ዓለም አቀፍ የዜና ወኪል አረጋግጠዋል። ይሁን እንጂ ይህንን ውንጀላ ሁለቱም አካላት አጥብቀው አስተባብለዋል። የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል ጄኔራሉ የሰጡትን መግለጫ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ያደረጉ ሲሆን፤ በሕወሓት በኩልም ምክትል ሊቀመንበሩ አማኑኤል አሠፋ የድርጅቱ አመራሮች አሁንም ትግራይ ውስጥ በሥራ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።