← All news
News Oct 21, 2026 · 17d ago

በመቐለ ከተማ ለህወሓት ታጣቂዎች ተዘጋጅቶ የነበረ የምግብ ክምችት በህብረተሰቡ ጥቆማ ተያዘ

በመቐለ ከተማ ለታጣቂዎች ቀለብ ተብሎ በመጋዘን ተከማችቶ የነበረ የምግብ ፍጆታ በሕብረተሰቡ ጥቆማ መሠረት በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ። በመንደር ውስጥ በሚገኝ መጋዘን የተከማቹ በርካታ ካርቶኖች ዘይት፣ ኮቾሮ እና ስኳር መገኘታቸውን የተገለጸ ሲሆን፣ ከተያዙት የምግብ እቃዎች መካከል በግብፅ የተመረተ ስኳርም እንደሚገኝ ተጠቁሟል። እንደደረሰን መረጃው፣ እቃዎቹ ለታጣቂዎች ቀለብ ተብለው ተከማችተው እንደነበር ተገልጿል።ህወሓትን በኤርትራ መንግስት አማካኝነት የምትደግፈው ግብፅ ከጦር መሳሪያ ፣ ከስልጠና እና ተልዕኮ ከመስጠት ባለፈ ለታጣቂዎች ቀለብ በመስጠትም የህወሓት ቡድን ኢትዮዺያን ለማዳከም የተሰጠውን ስራ እያገዘች እንደነበር ማሳያ ነው።