የሰቲት ሁመራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ
የብፁዕ አቡነ ሉቃስ ማረፍን አስመልክቶ ዛሬ ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ከቅዱስ ሲኖዶስ መክፈቻ ሥርዓተ ጸሎት ጋር በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ መሪነት ይፈጸማል። የሌሊቱ ሥርዓተ ፍትሐት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይቀጥላል። የብፁዕ አቡነ ሉቃስ ግብዓተ መሬት ነገ ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከቅዳሴ በኋላ ይፈጸማል።