← All news
News Oct 21, 2026 · 17d ago

የስጋ ዋጋ ጉዳይ‼️

በአዲስ አበባ የስጋ ዋጋ ማስተካከያ ለማድረግ ከልኳንዳ ቤት ባለቤቶች ጋር ውይይት ተካሄደ ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ የሚስተዋለውን ያልተገባ የስጋ ዋጋ ጭማሪ ለመቀነስ እና ከህብረተሰቡ የመግዛት አቅም ጋር ያገናዘበ የዋጋ ማስተካከያ ለማድረግ የሚያስችል የውይይት መድረክ ተካሄደ። የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ እና የከተማዋ ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በጋራ በካሄዱት በዚህ መድረክ፣ በስጋ ንግድ ዘርፍ ባለው የዋጋ ሁኔታ ላይ የተሰራ የዳሰሳ ጥናት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል። በውይይቱ ወቅት የልኳንዳ ቤት ባለቤቶች በበኩላቸው በቁም ከብት ግብይት ሂደት ውስጥ የደላሎች ጣልቃ ገብነት ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ መሆኑን በመጥቀስ፣ መንግስት ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። የንግድ ቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በሰጡት ምላሽ፣ በአሁኑ ወቅት የቁም ከብት አቅርቦት እጥረት በሌለበት ሁኔታ የታየው ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ተቀባይነት እንደሌለው ገልጸዋል። አያይዘውም የከተማ አስተዳደሩ የልኳንዳ ቤቶች በቀጥታ ከአርሶ አደሮች ጋር የሚገናኙበትን የገበያ ትስስር ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሰራ ጠቁመዋል። gursha