← All news
News Oct 21, 2026 · 17d ago

አሜሪካ በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ጉዳይ በድጋሚ አስጠነቀቀች!

ዜጎቿ ከሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች እንዲወጡ አሳስባለች አሜሪካ በሰሜን ኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ክልል የተቀሰቀሰው ግጭት በማንኛውም ሰዓት ሊባባስ ይችላል በማለት አስጠንቅቃለች። በአዲስ አበባ የሚገኘው የሀገሪቱ ኤምባሲ በዛሬው ዕለት ለአሜሪካውያን ባስተላለፈው የጥንቃቄ መልዕክት፡ ለማንኛውም ጉዳይ ወደ ትግራይ፣ አማራ አና አፋር ክልሎች እንዳይጓዙ አሳስቧል። አሁን ላይ በተለይም በትግራይ እና አፋር ክልሎች ወታደራዊ ግጭቶች መቀነሳቸውን የገለጸው ኢምባሲው፤ ሆኖም ዳግም ሊባባስ እንደሚችል አስጠንቅቋል። በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኙ ዜጎቹም አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ አሳስቧል።