← All news
News Oct 21, 2026 · 18d ago

ልዩ መረጃ‼️

በኢትዮ ኤርትራ ድንበር ሰላም አስከባሪ ኃይል እንዲሰማራ ኤርትራ መጠየቋ ተሰማ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ወደ ኬንያ ከመጓዛቸው ቀደም ብሎ October 18/2026 የኤርትራ ባለስልጣናት ወደ ናይሮቢ ተጉዘው እንደነበር ተረጋግጧል። የኤርትራ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ እና የማነ ገብረአብ ከቀናት በፊት ወደ ናይሮቢ ተጉዘው እንደነበር የዲፕሎማቲክ ምንጮች አረጋግጠዋል። በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒሰትር አብይ አሕመድ የማሹጃ ቀንን ለማክበር በእንግድነት ተጋብዘው በትናንትናው እለት ወደ ኬንያ ማምራታቸው ይታወቃል። እንደ ምንጮቹ ገለጻ ሁለቱ የኤርትራ ቁልፍ ባለስልጣናት ወደ ኬንያ የተጓዙት በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ውይይት እንዲጀመር ኬንያን ሎቢ ለማድረግ ነው ተብሏል። ሻብያ በሁለቱ አገራት ውጥረት ኬንያ እንድታደራድር ፍላጎት እንዳለው የተገለጸ ሲሆን፤ በድንበሩ ላይ ሰላም አስከባሪ ኃይል እንዲሰማራ ፍላጎቱን መግለጹ ታውቋል። ኤርትራ ከሁለቱ አገራት መካከል ባሉ የድንበር አካባቢዎች የሰላም አስከባሪ ኃይሎች እንዲሰማሩ ሀሳብ አቅርባለች። ይህም ከአልጀርስ ስምምነት በኋላ ውጥረትን ለማርገብና ጦርነትን ለመከላከል እንደተደረገው ዓይነት እርምጃ ነው። ሆኖም፣ ኢትዮጵያ ይህንን ሀሳብ መቀበል ወይንም አለመቀበሏን በተመለከተ የተባለ ነገር የለም።