← All news
News Oct 20, 2026 · 18d ago

በመቐለ ከተማ የኮሪደር ልማት ሥራ በቅርቡ ይጀመራል

በመቐለ ከተማ የኮሪደር ልማት ሥራን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አካላት ጋር ውይይት መካሄዱን የከተማዋ ከንቲባ ዶ/ር ሽሻይ አስታወቁ። ከንቲባው እንዳሉት፣ ከኮሪደር ልማቱ ጋር በተያያዘ ትናንት ከሰዓት በኋላ የተካሄደው ውይይት የመጀመሪያ ዙር ሲሆን፣ የልማት ሥራው በቅርቡ ወደ ተግባር እንደሚገባ ገልጸዋል። በመቐለ ከተማ የኮሪደር ልማቱ በፍጥነትና በጥራት እንዲከናወን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጥብቅ መመሪያ መስጠታቸውም ተገልጿል።