የትግራይ ክልል የመንግስት ሰራተኞች ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ።
የትግራይ ክልል ባለአደራ መንግስት ሁሉም የመንግስት ሰራተኞች ከዛሬ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሶስት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በሚሰሩበት መስሪያ ቤት በአካል በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል። በተጠቀሱት ሶስት የስራ ቀናት ውስጥ በአካል ተገኝቶ ሪፖርት የማያደርግ ማንኛውም ሰራተኛ ለሚተላለፈው ውሳኔ ራሱ ሀላፊነቱን እንደሚወስድ ተገልጿል። በተጨማሪም በየመስሪያ ቤቱ የሚገኙ የሰው ሀይል አስተዳደር አስተባባሪዎች በተቋሞቻቸው በአካል በመገኘት የሰራተኞችን መገኘት እንዲመዘግቡ ማሳሰቢያ ተላልፏል።